1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት መግለጫ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 14 2014

የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎችን ያጣመረ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የሚተገበር ሕግ የማስከበር ርምጃ እንደሚወሰድ መንግሥት ተናገረ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ በመንግሥት ይወሰዳል የተባለው ርምጃ «ሁሉን ባቀፈ መልኩ የሚከወን የተቀናጀ እና የተደራጀ» ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4AJ0D
Äthiopien | Dr. Legesse Tulu - Kommunikationsminister
ምስል Seyoum Getu/DW

«ተገቢው ርምጃ ይወሰዳል»

የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎችን ያጣመረ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የሚተገበር ሕግ የማስከበር ርምጃ እንደሚወሰድ መንግሥት ተናገረ። የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፀጥታ እና ደኅንነት ሁኔታ አስመልክቶ ከተወያየ በኋላ ዛሬ ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ ለዶይቼ ቬለ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ በመንግሥት ይወሰዳል የተባለው ርምጃ «ሁሉን ባቀፈ መልኩ የሚከወን የተቀናጀ እና የተደራጀ» ነው ብለዋል። ይህንኑ ለመፈፀም የተለየ የወጣ ሕግ ስለመኖር አለመኖሩ የተጠየቁት ሚኒስትሩ መንግሥት በሕገ ምንግሥቱ የተሰጠውን ሥልጣን ከመጠቀም በዘለለ አዲስ የተቀመጠ ሕግ አለመኖሩን ተናግረዋል። የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት፦ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ሰላም የሚነሱ፣ የመሬት ወረራ እና ማታለል የሚፈጽሙ፣ እንቅስቃሴን የሚያውኩ፣ የልማትና የኢንቨስትመንት ተግባራትን የሚያደናቅፉ እና የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጽሙ ባላቸው አካላት ላይ «ተገቢው ርምጃ ይወሰዳል» ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ