ማስታወቂያ
በሄይቲ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንሥትር አሪዬል ሔንሪን ለማስወገድ የዛቱ አመጸኛ ወንበዴዎች በዋና ከተማዪቱ ዛሬም ውጊያቸው አጠናክረዋል ። ትናንት ዋናውን የሀገሪቱን የአየር መንገድ ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ተዋግተው ነበር ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ ከሥልጣናቸው መውረድ የነበረባቸው ባለፈው ወር ነበር ። የታጠቁ ወረበላ ቡድኖች ዋና ከተማዪቱ ፖርት ኦ ፕሪንስ ውስጥ በሚገኘው አየር መንገድ፤ እስር ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የተቀናጀ ጥቃት ከፍተዋል ።
የወረበሎቹ ቡድን መሪ ጠቅላይ ሚንሥትሩን «እስከመጨረሻ ደም ጠብታችን እንፋለማለን» ሲሉ መዛታቸው ምናልባትም ሄይቲ ወደ ከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳትገባ አስግቷል ።
ሄይቲ ከ11 ሚሊዮን ትንሽ ከፍ ለሚል ነዋሪዋ 9,000 ግድም ፖሊሶች ብቻ ናቸው ያሏት ። ሄይቲ ሁከት ትርምሱን ለመቆጣጠር የተሳናትም ትመስላለች ።
ቪዲዮ ዘገባ፦ ዶይቸ ቬለ (DW)
ምንጭ፦ አሶሺዬትድ ፕሬስ