1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ መሪዎች ከሶማልያ የዉጭ ኃይላትን ሁሉ ሊያስወጡ ነዉ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 21 2015

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በሶማልያ ያሰማራቸዉን የሰላም አስከባሪ የውጭ አገር ወታደሮች ሁሉ ደረጃ በደረጃ ለማውጣት ተስማምቷል። ህብረቱ የሰላም አስከባሪ ጓዱን ማስወጣት የሚጀምረው ከፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሆንም ይጠበቃል። ይሁንና የዉጭ ኃይላቱን የማዉጣቱ ሂደት የሶማሊያን ዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥስ አይገባም።

https://p.dw.com/p/4Qgmh
AMISOM Soldaten aus Burundi in Mogadischu
ምስል Ilyas A. Abubakar/AU UN IST Photo/AFP

በሶማልያ የራስዋን የፀጥታ ኃይላት የማሰልጠን አቅም አላት

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በሶማልያ ያሰማራቸዉን የሰላም አስከባሪ የውጭ አገር ወታደሮች ሁሉ ደረጃ በደረጃ ለማውጣት ተስማምቷል። ህብረቱ የሰላም አስከባሪ ጓዱን ማስወጣት የሚጀምረው ከፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሆንም ይጠበቃል። የአፍሪቃ ህብረት ባወጣዉ የአቋም መግለጫ ይፋ የሆነዉ በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ላይ የአፍሪቃ ሃገራት የዉጭ ጉዳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የልማት አጋሮች ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ ነው። 

ለአፍሪቃ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ወታደሮች ያዋጡ ሀገራት የመከላከያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና አጋር ሃገራት የአፍሪቃ ኅብረት ወታደሮች በሶማሊያ የሚታየዉ የፀጥታ ሁኔታ ሳይደፈርስ በተቀናጀ ሁኔታ ከሶማሊያ እንዲወጡ ጠይቀዋል።  በጥሪዉ መሰረት እስከ ፊታችን ሰኔ 23 እለት ድረስ  2,000 ወታደሮች ሶማልያን ለቀዉ ይወጣሉ ። 

Symbolbild I Soldaten Burundi
በሶማልያ ተሰማርተዉ የሚገኙ ኃይላት ምስል Mohamed Abdiwahab/AFP/Getty Images

በስብሰባው ወቅት የዩጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጄጄ ኦዶንግ የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች ከሶማሊያ በተሳካ ሁኔታ ለመውጣት ተገቢውን እቅድ ለማመቻቸት ስብሰባው በወሳኝ ወቅት መካሄዱን ተናግረዋል።  

«ወታደሩን ለማዉጣት ገቢራዊ የሚደረግበትን የጊዜ ሰሌዳ እና የሶማሌያ ፌደራል መንግሥት የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ  በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ እና ኃላፊነትን እንዲሸከም ለማድረግ በእቅድና በቅንጅት በጋራ ግምገማ ማስፈፀሙ ይመከራል። ስለዚህም ይህ ስብሰባችን በሶማሊያ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለመገምገም  የተገኙትን ስኬቶች ለማየት ጊዜዉ ወሳኝ ነው።» 

የአፍሪቃ ህብረት በሶማልያ ያሰማራዉን የፀጥታ ጓድ ለማስወጣት ቢስማማም፣ የሶማልያ ጎረቤት ሀገራት በሶማሊያ ውስጥ ስላላቸው ቀጣይ ሚና አሳስበዋል።  የኬንያ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤደን ዱዓሌ በቀጠናዉ ሰላምና ፀጥታን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አስምረዉበታል። 

Horn von Afrika Hungersnot
የሶማልያ ኃይላት ምስል picture-alliance/dpa

«የአካባቢ እና ዓለም አቀፍ የደህንነት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በየጊዜው በፍጥነት እየተለዋወጠ ለአዳዲስ አዝማሚያዎች እና ፈታኝ ሁኔታዎች እየተጋፈጥን ነዉ። ስለዚህም የበለፀገ ኢኮኖሚን ለማግኘት  በአካባቢያችን ሰላም፣ ደህንነትና መረጋጋት እንዲሰፍን የማድረግ ሃላፊነት አለብን።» 

 በአፍሪቃ ህብረት የግጭት አፈታት ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ዳይሬክቶሬት፣አልሃጂ ሳርዮህ ባህ በሶማልያ የተሰማሩትን የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪን የማዉጣቱ ጉዳይ የሶማሊያን ሰላማዊ ዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥስ አይገባም ይላሉ።  

« አፍሪቃ ህብረት በጸጥታ ምክር ቤቱ ውሳኔዎች መሰረት እቅዱን ውጤታማ በሆነ መንገድ ግባራዊ ለማድረግ በቁርጥ ውሳኔዉ ቀጥሏል። ይሁን ይህ እንዲሳካ ሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይኖር ለማረጋገጥ ተቀናጅተን መስራታችንን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው። በዚህ ልዩ ጥረት ወታደሮችን ያዋጡ ሃገራት መካከልም ስምምነት መኖሩ አስፈላጊ ነው።» 

  ሳርዮህ ባህ በአፍሪቃ ህብረት የግጭት አፈታት ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ዳይሬክቶሬት፣አልሃጂ በጎርጎረሳዉያኑ 2022 ዓም በሶማልያ ዳግም የታደሰውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ  የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤትን ጠይቀዋል።  በተመሳሳይም ኤስ ኤስ ኤፍ ያገኛትን የጋራ ትርፍ ጠብቆ ለማቆየት ያለው ልዩነት በጣም አስፈላጊ ነው።

Symbolbild I Soldaten Burundi
በሶማልያ ተሰማርተዉ የሚገኙ ኃይላት ምስል Mohamed Abdiwahab/AFP/Getty Images

"በተመሳሳይም፣ ኤስ ኤስ ኤፍ ያገኛትን የጋራ ትርፍ ለማስቀጠል ያለው ልዩነት ነው። በዚህ ምክኒያት አፍሪቃ ህብረት ሶማሊያ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ጥሪውን በድጋሚ ለማቅረብ ይፈልጋል። ሶማሊያ  በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2662 በተዘረዘሩ ወሳኝ መመዘኛዎች ላይ መሻሻል እንድትቀጥል ። ይህ አሁን ወቅታዊ ጥያቄ ሳይሆን የሞራል ጥያቄ ነው።" 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የክልሉ ሃገራት መንግስታት ሶማሊያ አሁን በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ደህንነት ለማስረከብ የራሷን ኃይሎች መመልመልና ማሰልጠን ትችላለች ብለው ያምናሉ።

አዜብ ታደሰ

ነጋኅ መሐመድ