1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ግጭት የተኩስ አቁም ጥሪ በአፍሪቃ ኅብረት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 11 2015

በኢትዮጵያ መንግስት እና በአማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች ባላቸው አካላት የተፈጠረው እና የብዙዎችን ሕይወት ቀጥፎ በርካቶችን ለጉዳት ያጋለጠው ግጭት እንዳሳሰበው እና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ የአፍሪቃ ኅብረት ጠየቀ።

https://p.dw.com/p/4VHnw
የአፍሪቃ ኅብረት አርማ እና ተሰብሳቢዎቹ
የአፍሪቃ ኅብረት አርማ እና ተሰብሳቢዎቹ። የአፍሪቃ ኅብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ኢትዮፕያ ይገኛል ። በዚህ አዳራሽ ውስጥ የአፍሪቃ ኅብረት መሪዎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ በተለያዩ ጊዜያት ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ። ፎቶ ከማኅደርምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

በኢትዮጵያ መንግስት እና በአማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች ባላቸው አካላት የተፈጠረው እና የብዙዎችን ሕይወት ቀጥፎ በርካቶችን ለጉዳት ያጋለጠው ግጭት እንዳሳሰበው እና  ችግሩ በውይይት እንዲፈታ የአፍሪቃ ኅብረት ጠየቀ። 

ሕብረቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የተከሰተውን ጦርነትና የፀጥታ ችግር ለመቀልበስ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ ባወጣው መግለጫው የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርበት እና በከፍተኛ ሥጋት እየተከታተሉት መሆኑን ገልፀዋል። 

በሀገሪቱ እና በአካባቢው መረጋጋትን ለማረጋገጥ የአፍሪቃ ኅብረት ከኢትዮጵያን ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት፣ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ጋር ያለውን ትስስር እንደሚያረጋግጥ የገለፀት ፋኪ ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና የዜጎችን ከለላ እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል። 

ሕብረቱ ያቀረበውን ጥሪ መነሻ በማድረግ ያነጋገርናቸው አንድ የአለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ተንታኝ "በአፍሪካ ሕብረት በኩል እድገት እያዩ" መሆኑን ገልፀው ነገር ግን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ግልጽ አለመሆን አሁን ለተፈጠረው ግጭት መነሻ ምክንያት መሆኑን አስረጂ በመጥቀስ ሕብረቱ "ግጭትን ሊያስነሳ በማይችል መልኩ ድርድርን ማመቻቸት የማይችል ነው" ብለዋል።// 

የአፍሪቃ ኅብረት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈንየሚደረገውን ተነሳሽነት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ ባወጡት መግልጫ አረጋግጠዋል። ግጭቱ እንዳሳሰባቸው የገለፁት ፋኪ ጉዳዩ በውይይት እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል። 

አሁን ያለው ግጭት በትግራይ ከነበረው ግጭት በመሠረታዊነት የሚለይባቸው ባህርያት አሉት ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ፣ የትግራዩ አስቀድሞ መንግሥት የነበረ አካል አሁን ካለው መንግሥት ጋር ያደረጉት ፣ አሁን በአማራ ያለው ግን አስቀድሞ መንግሥት ከነበረ አካል ጋር  ሳይሆን የሕዝብ በሆነ ኃይል እና በመንግሥት መካከል የሚደረግ ግጭት ነው ብለዋል። በትግራይ የነበረውን ጦርነት የሚመራው የታወቀ አካል ነበር ያሉት እኒሁ ሰው የአማራው ግን የተደራጀ አይደለም ማለት ባይቻልም ማዕከላዊ እና ይሄ ነው ተብሎ የሚመራው አካል የሚጠቀስለት አይደለም ብለዋል።
"የትግራዩ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ ነበራቸው። የቅቡልነት ጥያቄ ላይ የተነሳ ጥያቄ ነው የነበረው። ይሄኛው ግን የቅቡልነት ጥያቄ አይደለም አስቀድሞ የመጣው። አስቀድሞ የመጣው የመተማመን ጥያቄ ነው" 
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ያስከተላቸው ችግሮች የአፍሪካ ሕብረት አሁን ላቀረባቸው የሰላም ጥሪዎች መተማመኛ የሚነፍጉት ጉዳዮች ስለማስከተላቸው እኒሁ ሰው ገልፀዋል።

ፕሪቶሪa፦ የተኩስ አቁም ስምምነት በኢትዮጵያ
ፕሪቶሪa፦ የተኩስ አቁም ስምምነት በኢትዮጵያ ። ከግራ ወደ ቀኝ ፎቶው ላይ የሚታዩት፦ የደቡብ አፍሪቃ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚንስትር ናሌዲ ፓንዶር፤ ሬድዋን ሁሴን፤ የኢትዮፕያ መንግሥት ተወካይ፤ የኬንያ ፕሬዚደንት ዑኹሩ ኬንያታ፤ የአፍሪቃኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዑክ የናይጄሪያው ፕሬዚደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፤ ጌታቸው ረዳ፤ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ተወካይ፤ እንዲሁም የደቡብ አፍሪቃ ምክትል ፕሬዚደንት ፑምዚሌ ምላምቦ-ንጉካ በአፍሪቃ ኅብረት መር የሰላም ስምምነት የሰላም ስምምነት ወቅትት ለፎቶ ተደርድረውምስል PHILL MAGAKOE/AFP

"የፕሪቶሪያ ስምምነትራሱ አሁን ላለንበት የቀውስ ሁኔታ መንገድ ከፍቷል። የግልጽነት ችግር ስለነበረበት። ሕብረቱ ሌላ ግጭት ሊያስነሳ በማይችል ምልኩ ድርድርን ማመቻቸት ይችላል የሚል እምነት የለኝም ። ምክንያቱም በትግራይ ኃይሎች እና በመንግሥት በኩል ያደረገው የማደራደር ሥራ ለሌላ ችግር ጥንስስ ሆኖ ስላገለገለ ነው" ብለዋል። ይህ ሲባል ግን የሕብረቱ ጥረት ሙሉ በሙሉ የሚናቅ እንዳልሆነም ተንታኙ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ፤ የአፍሪቃ ኅብ,ት ጉባኤ በአዲስ አበባ ።
ኢትዮጵያ፤ የአፍሪቃ ኅብ,ት ጉባኤ በአዲስ አበባ ። የአፍሪቃ ኅብረት መሪዎች በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለጉባኤ በተሰበሰቡበት ወቅት የተነሳ ፎቶግራፍ ። ከፎቶ ተነሺዎቹ ጀርባ የአፍሪቃ ኅብረት አርማ ጎላ ብሎ ይታያል ። ፎቶ ከማኅደርምስል Solomon Muchie/DW

"በአፍሪካ ሕብረት በኩል እድገት እያየሁበት ነው ብየ እወስዳለሁ። በእንደዚህ አይነት ገዳዮች ላይ ምንም የማይል ተቋም ነበር። ይሄ ተቋም በትግራይ የተዋጣ ሥራ ሠርቷል።
አሁንም እንደዚህ አይነት ነገሮችን የመቀጠል እድል አለው።" 

በመንግሥት እና በፋኖ መካከል በአማራ ክልል የተደረገው ግጭት በዘላቂነት በሰላም እንዲፈታ ብዙ የምዕራብ ሀገራት፣ የተለያዩ የሀገር ውስጥ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች በመወትወት ላይ ናቸው።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ